(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥር 11 ቀን 2005 ዓ.ም.) ለዛሬ ስለ ሁለት ዋልያዎች እንጽፋለን
- የኢትዮጵያችን የብቻዋ ስለሆነ እንስሳው ዋልያና ዋልያ ተብሎ ስለሚጠራው ብሔራዊው የእግር ኳስ ቡድናችን። በተለይ ስለ ሁለተኛው
ዋልያ ለመጻፍ ወይም መጻፍ ለመጀመር ዛሬ ምቹ ነው። ብሔራዊ ቡድናችን የያዘውን መጠሪያ ስም ያገኘው ከብርቅየው እንስሳ ‘ዋልያ
አይቤክስ’ ስም ነው። የአሰያየም ሂደቱ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ የለኝም (እነ ደጉ፤ አዳነና ጀማልም አናውቀውም ሲሉ ሰምቻለሁ)።
ዋልያ አይቤክስ የኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሊሆን እንደሚችል ግን መገመት ይቻላል። ስለ ሁለቱም ዋልያዎች (ዋልያ
ዘሜዳና ዋልያ ዘኳስ) በተራበ ተራ (አሁን ባይርበኝ ኖሮ ‘በተራ በተራ’ ብዬ እጽፈው ነበር) እናነሳና ከዛም መልሰን እናገናኛቸዋለን።
Tuesday, January 22, 2013
እነሱ ከእኛ ወይስ እኛ ከነሱ?
(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥር 4 ቀን 2005 ዓ.ም.) በውጪው ዓለም ገና እና አዲስ
ዓመት በስድስት ቀናት ልዩነት የሚከሰቱ ሁለት በዓላት ሲሆን መዘዛቸው ደግሞ እጅግ ከፍተኛ ነው። በምዕራቡ ዓለም የገና በዓል ከጊዜ
ወደ ጊዜ ትርጉሙም ሚናውም እየተቀየረ መምጣቱን ማየት ይቻላል። እዚህ ካናዳ ውስጥ በአንድ ትምህርት ቤት ህጻናት ከቤተሰቦቻቸው
ለተለያያ ትውልድ የገና በዓል የሚሰጠው ትርጉም ምን እንደነበር ጠይቀው እንዲጽፉ የቤት ስራ ይሰጣቸዋል። አንዱ ቅድመ አያቱን አያቱንና
አባቱን ጠይቆ መጣ። ሴቷ ቅድመ አያቱ በዘመናቸው ጊዜ የነበረውንና የገና ብስኩት ላይ ስለሚቀባው ክሬም አንስተው ለዛን ዘመን ውድ
ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለገና ብቻ ተቀብቶ ስለሚበሉት እንዴት በጉጉት ይጠብቁት እንደነበርና ያኔ የሰፈር ሰዎች አንድ ላይ ሆነው
ያከብሩ እንደነበር አጫወቱት። አባታቸው ሚንስተር የነበሩት አያቱ ደግሞ የገና በዓል ለሳቸው ዘመን ሰዎች ጎዳና ተዳዳሪዎችን የመርጃ፤
ቤተ ክርስቲያን ሄደው ዝማሬ ማቅረቢያና ጎረቤታሞች ምግብና ደስታ የሚጋሩበት እርስ በርስ እየተደጋገፉ የሚያከብሩበት በዓል እንደነበር
ነገሩት። አባቱን ሲጠይቅ ያገኘው መልስ ደግሞ የገና በዓል አከባበር ሌላ ቅርጽና ይዘት መምጣቱን ማየት የሚያስችል ነበር። አባትዬው
ስለ አሻንጉሊቶችና ትልልቅ የፕላስቲክ መጫዎቻዎች እንደስጦታ መስጠት ዋነኛው የበዓሉ መገለጫ እየሆኑ መምጣታቸውንና ከዚህም ጋር
በተያያዘ ወላጆች ስጦታዎችን ለመግዛት አቅም በሚያጡበት ጊዜ እንዴት
ጫናም ሀዘንም ይሰማቸው እንደነበር አጫወቱት።
Tuesday, January 8, 2013
ከጤንነት የሚሻል ሕክምና የለም
(ጌታቸው አሰፋ፤ ታኅሣሥ 20 ቀን 2005 ዓ.ም.) ዛሬ የምጽፍበት ጉዳይ ከአረንጓዴ
ጉዳይ ጋር ምን አገናኘው ለምትሉ አስቀድሜ መልስ ልስጥ። በአካባቢ ጥበቃም ሆነ በኃይል አቅርቦትና ፍጆታ ዙሪያ በአገሪቱ መዋዕለ
ንዋይ ፈሶባቸው የሚሰሩ ስራዎች ወጪ ቆጣቢ ሆነው ውጤታማ እንዲሆኑ ካስፈለገ ከእውቀት አኳያ አንዱን ሳይጥል ሌላውን ሳያንጠለጥል
መሆን አለበት። ከዚህ በላይ ደግሞ የማንኛውም አገር ልማታዊ ጉዞ በእውቀት ላይ መመስረት አለበት። በዚህ ሁሉም ሰው ከሞላ ጎደል
ይስማማል። እውቀት ደግሞ ከመማር ይገኛል። በዚህም ብዙ ልዩነት አይኖርም። ጥያቄ የሚነሳው ግን ‘መማር ምን ማለት ነው?’ ‘ሰው
የትና ከማን ይማራል?’ ‘ከየትና ከማንስ መማር አለበት?’ በሚሉት ዙሪያ ላይ ነው። በአገራችን በየእርከኑ መደበኛ ትምህርት ቤትና
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብቶ የሚማረው ሰው ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ይገኛል። ለፈጣንና አዛላቂ እድገት የተማረ ሰው
ቁጥር መጨመሩ አስፈላጊ ነውና ደግ ነው።
Friday, December 21, 2012
ለመስማማት መስማማት?
(ጌታቸው አሰፋ፤ ታኅሣሥ 6 ቀን 2005 ዓ.ም.) የዶሃው የአየር ንብረት ጉባኤ
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ተጠናቋል። በጉባኤው ላይ ተስፋ አልነበረኝም። ከተጠናቀቀ በኋላም የሚያስደስት ነገር አላገኘሁበትም። ውሳኔዎች
ግን ተላልፈዋል - ጥርስ ይኑራቸው አይኑራቸው በጊዜ የምናያቸው። ከውሳኔዎቹ ጥቂት የማይባሉት ከአሁን በፊት በነበሩት ጉባኤያትም
የተላለፉ ነበሩ። ስላልተገበሩ ግን አሁንም ‘እናረጋግጣለን’ እና ‘እናጠናክራለን’ ወዘተ የሚል ተጨምሮባቸው ተመልሰው መጥተዋል። እስቲ የውሳኔውን ዋና ይዘት እንየው።
ልቀቁልን እንጂ አትልቀቁብን - ዶሃ
(ጌታቸው አሰፋ፤ ኅዳር 29 ቀን 2005 ዓ.ም.) የአየር ንብረት ለውጥን እንደ
ገዳይ በሽታ ብንቆጥረው ኖሮ ዓለም መታከምና መዳን አለባት የሚለው ላይ እንስማማና ወደ ተግባር እንሄድ ነበር። በዚህ እሳቤ የካርበን
ልቀት በሽታ አምጪ ታህዋስያን ልቀት ተደርጎ ከታሰበ ልቀቱ ሲሆን ፈጽሞ እንዳይኖር ካልሆነም በእጅጉ እንዲቀንስ እናደርግ ነበር።
ችግሩ ግን በነባራዊው ዓለም የአየር ንብረት ለዋጭ ጋዞች ልቀት ገንዘብ ለማስገኘት በሚደረግ ሂደት የጎንዮሽ ተጽእኖ ሆኖ መከሰቱ
ነው። ሌላው ችግር ለቃቂዎች አቅም ያላቸው፤ የሚታመሙት ደግሞ አቅመ አናሳዎች። ቀመሩ ውስጥ ገንዘብና ኢኮኖሚ ባይኖሩበት ኖሮ ይህ
ሁሉ የጉባኤ ጋጋታም አያስፈልግም ነበር። ይህ አልሆነምና ስብሰባም ጉባኤም አለ። እነሆ የዶሃው ጉባኤም እንደቀጠለ ነው (ይህ ጽሁፍ
እስከተጻፈበት ጊዜ ድረስ)።
የዶሃው ጉባኤ
(ጌታቸው አሰፋ፤ ኅዳር 22 ቀን 2005 ዓ.ም.) ከዚህ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ በካታር
ዶሃ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ አስራ ስምንተኛው የባለድርሻዎች ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል። አምና በደርባን ደቡብ አፍሪካ
ተደርጎ የነበረው ጉባኤ ቀጣይ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥርስ ያለው ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስፈልጉ ነገሮች ሳይንስና ፓለቲካ
ናቸው። ሳይንሱ አሁንም በመረጃ እየደለበ እየሄደ ነው። እንዲያውም መሬት ላይ የሚታየው የአየር ንብረት ለውጥ አመልካች ክስተቶች
ሳይንስ ይሆናል ካለው ፈጥነው በርክተውና ጎልብተው እየታዩ ነው። በአሜሪካ የኸሪከን ሳንዲ የድርቅ ክስተት፤ የሰሚናዊ ዋልታዊ የበረዶ
ግግሮች ከልክ በላይ መቅለጥ፤ የባህር ጠለል ከፍ ማለት፤ የህንድ በኃይለኛ ጎርፍ መጥለቅለቅ፤ የሳህል አገሮች በከፍተኛ ድርቅ መመታት
ወዘተ።
Sunday, November 25, 2012
በሌለ በሬ ማረስ?
(ጌታቸው አሰፋ፤ ኅዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም.)ስለ ‘ያ ትውልድ’ና ‘ይሄ ትውልድ’ ከመጻፍ አስቀድሞ
‘ያ ትውልድ እና ይሄ ትውልድ ስንል ምን ማለታችን ነው?’ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ተገቢ ነው። በተለመደው አባባል በ1960ቹ መጀመሪያ
አጋማሽ ውስጥ ይካሄዱ በነበሩት የተማሪዎች እንቅስቃሴዎች ወቅት እድሜያቸው ቢያንስ ለአቅመ-መሳተፍ የደረሱ ሰዎች ስብስብን ነው
‘ያ ትውልድ’ የምንለው።
ላላ ስናደርገው ….የእድሜ መስፈርቱ እንዳለ ሆኖ
ቀጥሎ ያለውን አይነት ግጥም የሚገጥም ሰው ወይም እንዲህ ተብሎ የተጻፈ ግጥምን ማንበብ አሁን ድረስ የሚመስጠው ሰው አባል የሆነበት
ትውልድ ማለት ነው ልንልም እንችላለን።
ኦባማና የእጅ ነሺዎች አሜሪካ
(ጌታቸው አሰፋ፤ ኅዳር 7 ቀን 2004 ዓ.ም.)የአሜሪካው ምርጫ እነሆ ተጠናቀቀ።
ፕሬዚደንት ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠዋል። አንቱ የተባሉ ተንታኞች፤ ዋና ዋና የቅድሚያ ግምቶች የሚሰጡ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ሊባል
በሚቻልበት ደረጃ ምርጫውን ማን እንደሚያሸንፍ ለመተንበይ አለመቻላቸው ግልጽ ነበር (ከናቲ ሲልቨር በስተቀር)። መጨረሻ ላይ አሸናፊ
ሲታወቅም በጣም በትንሽ ልዩነት እንደሚሆን ሲናገሩ ነበር።
ባለሦስት ስለቱ ኸሪከን
(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም.)በአሜሪካና በካናዳ ምስራቃዊ
ዳርቻ ከተሞች የዚህ ሳምንት ሰኞና ማክሰኞ እንደወትሮው አልሆኑም። በብዙኃን መገናኛዎች እንደተከታተላችሁት ሳንዲ ተብሎ በሚጠራው
ጋላቢ ማዕበል(ኸሪከን) ሚልዮኖች ለችግር ተጋልጠዋል። በውሃ ነፋስ እና እሳት ስለት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአትላንቲክ ውቅያኖስ
አካባቢ የሚከሰተውና ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ማዕበል ‘ኸሪከን’ ተብሎ ይታወቃል።
ይድረስ ለመንግሥት- ሞያ በልብም በግልጽነትም ነው።
(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥቅምት 23 ቀን 2004 ዓ.ም.)እነሆ አባያችንን ለመደገብ የተጀመረው
ታላቅ ፕሮጄክት ደጋፊም ነቃፊም የሚለውን እያለ ባሳለፈበትና ባለበት ሁኔታ ከአስር በላይ ወይም በትክክል ለመግለጽ አስራ አንድ
ፐርሰንት ያህሉ መጠናቀቁን መንግሥት እየተናገረ ነው። በሀዘንም በደስታም ምክንያት ለአንድም ቀን ቢሆን ስራው ሳይቋረጥ እየቀጠለ
መሆኑን ተነግሮናልና - ደስ ይላል። ደስታችንን እያጣጣምን መነሳት ያለበትን እናነሳለን።
ግብርናችን
(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም.) በአጼ ኃይለሥላሴ ትተዳደር የነበረችው
ኢትዮጵያ ሀያ ሰባት ሚልዮን ህዝብ ነበራት። ከሃያ አንድ ዓመታት
የዙምባቤ ቆይታ በኋላም ባለቤታቸውን ‘ጓድ ውባንቺ ቢሻው፤’ ብለው የሚጠሩት መንግሥቱ ኃይለማርያም የአገሪቱ ርእሰ ብሄር የነበሩ
ጊዜና ኢሰፓን በመሰርቱበት ዓመት አካባቢ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን አርባ
ሚልዮን ገደማ ነበርን። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የተረከቧት አገር ደግሞ ቢያንስ ሰማንያ ሚልዮን ሰዎችን ይዛለች።
ፍሰትና ብክነት
(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥቅምት 9 ቀን 2004 ዓ.ም.) በአንድ አገር አዛላቂ የምጣኔ ሀብታዊ ክንውንውታ ላይ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ፍሰቶች
አሉ። እዚህ ውስጥ የምናካትታቸው የቁስ፤ የመረጃ፤ የኃይል፤ የገንዘብ እንዲሁም የእንስሳት የእጽዋትና የሰው ፍ(ል)ሰት ናቸው።
እነዚህን ፍሰቶች በተገቢው መጠን ቦታና ጊዜ መጠቀም ስንችል ነው በምጣኔ ሀብታችን ላይ የሚኖራቸው በጎ ተጽእኖ ማጉላት የሚቻለው።
አለበለዚያ ብክነት ይከተላል። እስቲ አንድ በአንድ እንያቸው።
‘አረንጓዴ’ አብዮት
(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥቅምት 2 ቀን 2004 ዓ.ም.) ዓለማችን ከፓለቲካዊ አብዮቶች
(መነሻ ቃል፡ አበየ - ‘እምቢ አለ’) በተጨማሪ ሌሎች ዘመን ቀያሪ፤ ሂደት ለዋጭ አብዮቶችን አስተናግዳለች - የግብርና አብዮት ፤ የኢንዱስትሪ አብዮት ፤ የሳይንስ አብዮት፤
የዲጂታል አብዮት። እነዚህ አብዮቶች ‘አብዮት’ ያሰኛቸው ከዛ በፊት ግብርና ወይም ኢንዱስትሪ ወይም ሳይንስ ወይም ዲጂታላዊ እንቅስቃሴ
ወይም ስራ ስላልነበረ አይደለም። በመጠናቸውና በአይነታቸው ከተለመደውና ከነበረው አሰራርና አካሄድ ለየት ባለ መልኩ ሁኔታ ቀያሪ
በሆነ መገለጫ ግብርናው፤ ኢንዱስትሪው፤ ሳይንሱና የመረጃ ቴክኖሎጂው ስለተስፋፋና አገሮች ከተለመደው መንገድ ‘በእምቢታ’ ወጥተው
ወደ አዲሱ መንገድ ስለገቡ ነው ከአብዮት ጋር ተያይዞ የሚነገርላቸው።
አፕል እና አካባቢ
(ጌታቸው አሰፋ፤ መስከረም 25 ቀን 2004 ዓ.ም.) እነሆ አዲሱ ትውልደ-አይፎን
iPhone 5 ገበያ ላይ ውሏል። በየአገሩ በየከተማው ከሰው ሁሉ አስቀድሞ ለመግዛት የነበረው ወረፋ በአንዳንድ የምግብ እጥረት
ባለባቸው አገሮች ለምግብ ነው እንዴ ያስብል ነበር። በምእራቡ ዓለም ደግሞ በነጻ የሚታደል ነገር አለ እንዴ (መቼም እንደ ፈረንጅ
በነጻ የሚታደል ነገርን ለመቀበል በነጻነት የሚሰለፍ አይቼ አላቅም)።
የህልም መስመረኛ
(ጌታቸው አሰፋ፤ መስከረም 18 ቀን 2004 ዓ.ም.) በኢትዮጵያዊነቴ እንድኮራ የሚያደርጉኝ
ብዙ በርካታ ነገሮች አሉ። አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው (አንዴ ሳይሆን በተደጋጋሚ ያየሁት የአስተናጋጆቹ ለራሳቸው አገር
ሰው ያላቸው ከተገቢ በታችና አሳፋሪ መስተንግዶና አያያዝ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው)። የዛሬ ጽሑፍ ማጠንጠኛ ስለ ኩራት እንጂ ስለ
ሀፍረት አይደለም። አየር መንገዳችን ከዘመን ዘመን በተሻገረ ቁጥር ከእድገት ወደ እድገት የሚሸጋገር፤ ማለም የማያቆም፤ አልሞም
የሚፈጽም፤ በአቻነት መነጋገር፤ በአብሮነት መስራት የሚችል፤ለሌሎች አገሮች የሚተርፍ አቅም የገነባ ነው - ደስ ሲል። በቅርቡ ድሪምላይነር
(የህልም መስመረኛ) ተብሎ የሚታወቀውን ዘመናዊውን ቦይንግ 787 አውሮፕላን ገዝቶ በመረከብ ከዓለም አየር መንገዶች ሦስተኛ ሲሆን፤
በአገር ደረጃ ደግሞ ከጃፓን ቀጥሎ አገራችን ሁለተኛ ሆናለች።
በ2004 ዓ.ም.ጣራ ስር
(ጌታቸው አሰፋ፤ መስከረም 11 ቀን 2004 ዓ.ም.) እነሆ 2004 ዓ.ም. አለቀ።
ዓመቱን ከኢትዮጵያና ከዓለም የኃይልና የአካባቢ ጉዳዮች አኳያ በግርድፉ
እንቃኘው።
‘ብርቱው የአፍሪካ ተደራዳሪ - አፍሪካ በበርካታ ግንባሮች ታጣዋለች።’
(ጌታቸው አሰፋ፤ መስከረም 4 ቀን 2004 ዓ.ም.) በዚህ ሳምንት
በሞት የተለዩንን ክቡር አቶ መለስ ዜናዊን ከአዛላቂ ልማት አኳያ የነበራቸውን ሚና በጥቂቱ በማንሳት አስባቸዋለሁ።እንደአለመታደል ሆኖ እሳቸውም ሳይጽፉ ስላረፉ ወይም በሌሎች ስለሳቸው የተጻፉት ነገሮችም
ቢሆኑ በስልጣን ላይ በነበሩበት ዘመን የዕለት ተዕለት ውሎዋቸውን በሚያሳይ መልኩ በዝርዝር አይደለም። እናም ይህን ስጽፍ የምጠቀምባቸው
ምንጮች በስራ ዓለም ካወቅኋቸው አጋጣሚዎች በመነሳት ነው።
ስለጅምላ በጅምላ ለጅምላ
(ጌታቸው አሰፋ፤ ጳጉሜን 3 ቀን 2004 ዓ.ም.) አዲስ አበባ በጣም ሰፍታለች።
በርካታ መንገዶች ተሰርተዋል እየተሰሩም ነው - በማሳለጫዎችና በመሽሎኪያዎች እንዲሁም በመንገደ-ብዙ ድልድዮች እየተደገፉ ነው።
የመኪኖች ቁጥርም እንዲሁ። የመጓጓዣ ችግር ግን አሁንም እንዳለ ነው። በቁጥርና በጥራት የሚገለጽ። በተለየ በተወሰኑ መስመሮችና
ጊዜያት። የየራሳቸውም ሆነ የየመስሪያቤታቸው መኪኖች ከሚያሽከረክረውና
በአንጻራዊነት ጥቂት ከሚባለው የአዲስ አባባ ነዋሪ ውጪ ያለው ሰው ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ራሱንና ቁሱን ለማጓጓዝ
የሚጠቀመው በጅምላ መጓጓዣዎች ነው። የጅምላ መጓጓዣ ውስጥ ውይይት ታክሲዎች፤ ሚኒ ባስ ታክሲዎች፤ ከኮንትራት ውጪ የሚሰሩ ትንንሽ
ታክሲዎች፤ ሎንቺናዎች፤ የአንበሳ አውቶብሶችና የሃይገር አውቶብሶች ይካተታሉ። በቅርቡ በአዲስ አበባ ስራው የተጀመረው የቀላል ባቡር
መጓጓዣም የዚህ ክፍል ዋና አካል ነው።
ክረምትና በጋ
(ጌታቸው አሰፋ፤ ነሐሴ 19 ቀን 2004 ዓ.ም.) የአገራችን የደንና አረንጓዴ
ሽፋን ጉዳይ ክረምት ክረምት ሲታይ አማን ይመስላል። ለወትሮው ራሰ
በራ የሚመስለው የሰሜኑ ሜዳና ሸንተረርም ሳይቀር በስሱም ቢሆን በአረንጓዴ ቀለም የተቀባ እንዲመስል የሚያደረገው ክረምት ነው።
ክረምት ከበጋ አገር ምድሩ ሁሉ አረንጓዴ ማድረግ እንኳን ባይቻል
እና ባይጠበቅም ቢያንስ ትንሽ የማይባል የአገሪቱ ክፍል ወጥ የሆነ የደንና የሌላ አረንጓዴ ሽፋን እንዳይኖረው የሚደረግበት ምክንያት
ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም። ውኃና አልሚዎችን እስካለን ድረስ ይቻላል።
‘በረከተ መርገም’
(ጌታቸው አሰፋ፤ ነሐሴ 12 ቀን 2004 ዓ.ም.) ርዕሱን የተዋስኩት ተወዳጁ የስቶክሆልሙ
ኃይሉ ገብረዮሐንስ ወይም ኃይሉ ገሞራው ከዛሬ አርባ አምስት ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረበት ወቅት ከጻፈውና
‘በረከተ መርገም’ የሚል ርዕስ ከነበረው ግጥሙ ነው። ኃይሉ ገሞራው ደራሲ፤ገጣሚና ባለቅኔ ነው። በ‘በረከተ መርገም’ ያኔ ድሮ ያኔ በዓለማችን በተለያየ ዘመን በተለያየ ቦታ
ስለ ተፈለሰፉት የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንድ በአንድ ፈልሳፊዎቹንም እያነሳ ከተፈጠሩበት ዓላማ ጀርባ ስላላቸው ወይም ሊኖራቸው ስለሚገባው
ኅብረተሰባዊ ጠቀሜታ እየጠቆመ ቴክኖሎጂ በአግባቡ ስንጠቀምበት በረከት
ነው በድሃውና በሀብታሙ፤ በተማረውና ባልተማረው፤ በከተሜውና በገጠሬው፤ ‘ባለው’ እና ‘በሌለው’ መካከል ሰፊ ልዩነት የሚፈጠርና
ልዩነቱንም በጣም እያሰፋ የሚሄድ ከሆነ ደግሞ መርገም ነው ይላል።
በኃይሉ ገሞራው ‘በረከተ መርገም’ የትችት ስለት የሚተለተሉት በኅብረተሰባዊ ክፍሎች መካከል ያለን ልዩነት በማስፋት አንዱ ወገን
ለሌላው ወገን ባርያና አገልጋይ እንዲሆን የሚያደርገው ቴክኖሎጂ ብቻ ሳይሆን ቴክኖሎጂውን የፈጠረውም ሰው ጭምር ነው።
Subscribe to:
Posts (Atom)