(ጌታቸው አሰፋ, ኅዳር 9 ቀን 2004 ዓ.ም) ባለፈው ጽሑፍ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘውን ሳይንስ ተመልክተናል። ዛሬም በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ዙሪያ ነው የሚጻፈው። ከዘጠኝ ቀን በኋላ ማለትም የፊታችን ህዳር 18 17ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ባለጉዳይ አካላት ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ ይጀመራል። በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ የሚጠናቀቅ ከሆነ ጉባኤው እስከ ህዳር 29 ይቆያል። በአውሮፓ ህብረት ለረጅም ጊዜ ሲገፋበት የነበረው የሁለት ዲግሪ ሴንትግሬድ(ቅድመ ኢንዱስትሪ አብዮት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር) ቀይ መስመር
Friday, February 3, 2012
Saturday, November 12, 2011
350 የካርበን ዳይኦክሳይድ ፊኛዎች?
(ጌታቸው አሰፋ)ይህ ካለፈው የቀጠለ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚያጠነጥነው ጽሑፍ ነው። ለዛሬ ስለ ሳይንስ በተቻለ መጠን ቀለል አድርገን እናወራለን። የአየር ንብረት ለውጥ ማለት በዓለም ደረጃና በረጅም ጊዜ የሚታዩ የለውጥ መገለጫ የሆኑት የከባቢ አየር ሙቀት፤ የዝናብ መጠንና የመሳሰሉት መገለጫዎች መለወጥ ማለት ነው። በአንድ ቦታና በአጭር ጊዜ ያለው የአየር ሁኔታ ለውጥ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ሊገናኝም ላይገናኝም ይችላል።
የመስተዋታዊ ቤተ-ተክል ጠንቅ
የአየር ንብረት ለውጥ ሉላዊ ሞቅታ ተብሎም ይጠራል። ለውጡም የሚገለጸው በዓለም የከባቢ አየር አማካይ ሙቀት መጨመር ነው። በሌላ በኩል የመስተዋታዊ ቤተ-ተክል ጠንቅ ተብሎም ይታወቃል። ይህን ስም ያገኘው ግድግዳቸውና ጣራቸው ከመስተዋት ወይም ከፕላስቲክ ከሚሰሩት ለአትክልቶች ለአበቦችና ለመሳሰሉት ማልሚያ ከሚሆኑት ቤቶች ጋር በተያያዘ ነው። በነዚህ ቤቶች የፀሐይ
Saturday, November 5, 2011
የአየር ንብረት ለውጥና ፍኖተ ደርባን
(ጌታቸው አሰፋ)የዛሬውና የቀጣዩ ጽሑፌ ትኩረት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ይሆናል። ምክንያት - አለም አቀፉ አስራ ሰባተኛው የአየር ንብረት ለውጥ ባለጉዳይ አካላት ጉባኤ ከፊታችን ህዳር 18 እስከ ህዳር 29 በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ ስለሚካሄድ።
ላለፉት አስራ አራት ዓመታት የተካሄዱት አለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮች የሚያጠነጥኑት የኪዮቶ ፕሮቶኮል ተብሎ በሚጠራው ስምምነት ዙሪያ ነው። የኪዮቶ ፕሮቶኮል ባለ ሀያ ስምንት አንቀጽና ሁለት አባሪዎች ስምምነት ሲሆን ጃፓን በሚገኘው የኪዮቶ ከተማ ታህሳስ ሁለት 1990 ዓ.ም. የጸደቀ ነው።
Thursday, October 13, 2011
ባለአረንጓዴ ቀበቶ ጀግና
(ጌታቸው አሰፋ) ዛሬ ይህ አምድ ኬንያዊቷን ዋንጋሪ ማታይን ያስባል። ዋንጋሪ ሙታ ሜሪ ጆ ማታይ ከሰባ አንድ ዓመታት በፊት በሞኞች ቀን(April 1) የተወለዱ ልባም ሴት ነበሩ። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውንና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በስነ-ህይወት ከአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ በእንስሳት ጤና ሳይንስ ስነ-ብልት ጥናት ከናይሮቢ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል። እሁድ መስከረም አስራ አራት 2004 ዓ.ም. በሞት ተለዩን። ሥራቸው ግን ከመንደራቸው፤ ከአገራቸውና ከአህጉራቸው አልፎ ከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ እውቅናን ያገኘ ህያው ሥራ ሆኖ ይቀጥላል።
ቀመሩ እንዲሰምር
(ጌታቸው አሰፋ)ስለ ግብርና እጽፋለሁ - ለዛሬ። መንግሥት ሁለት የማዳበሪያ ፋብሪካዎችን እገነባለሁ ማለቱ ነው መነሻዬ። መልካም ዜና ነው። እስቲ ወደ ኋላ ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በላይ እንንደርደር።
ከአጼ ቴዎድሮስ ጋር ለአሥር ዓመታት በአገራችን የኖረ ስዊዘርላንዳዊው ሚሶንያዊ ቴዎፍሎስ ቫልድማየር በዚህ ወር ግን ከ153 ዓመታት በፊት ወደ አቢስኒያ ተጓዘ። ከአምስት ወር በኃላም ገባ። ይህ ከሆነ ከሀያ ስምንት ዓመታት በኋላም ስለአሥር ዓመት ቆይታው መጽሐፍ ጻፈ (የተሳሳቱ መረጃዎች ያሉበት)። በመጽሐፉ የዛሬው ጉዳዬ ስለሆነው እርሻችንና ተያያዥ ነገሮችን በተመለከተ የተጻፈውንና የተሳሳተ ነው የሚያስብል ነገር ያላገኘሁለትን ወደ አማርኛ እንዲህ መልሼዋለሁ።
በዓል - ከጓዳ እስከ አካባቢ
(ጌታቸው አሰፋ) እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ። ከአንድ ሁለት ሳምንት በፊት የሸገር ራዲዮ “ዳጉ አዲስ”ን እያዳመጥኩ ነበር- በኢንተርኔት የቀጥታ ስርጭት። ወንዶች ሴቶችን በቤት ሥራ ማገዝ አለባቸው ወይስ የለባቸውም በሚል ርዕስ ስር ከተለያዩ ወጣቶች ጋር ቃል ምልልስ ያደርጋሉ - ዳጉዎች። ሁለት ወንድ ወጣቶች ቤታቸው ውስጥ ሽሮ ወጥ ሲሠሩ ከፕሮግራሙ አዘጋጆች አንዱ ተገኝቶ አሠራራቸውን በድምጽ ለራዲዮ አድማጮች ያስተላልፋል። ልጆቹና ጋዜጠኛው እያወሩ ከጀርባቸው አንድ አውራ ዶሮ ድምጹን ከፍ አድርጎ አሰምቶ ይጮሃል። የአሥር ወር ልጄን አየሁት። እየጮኸ ያለው አውራ ዶሮ መሆኑን ሊያውቅ እንደማይችል አሰብኩ። የእሱ አስተዳደግ በአካል ከሚታይ አውራ ዶሮ ጋር ያለው ርቀት የኔ አስተዳደግ ከአውራ ዶሮ ጋር ከነበረው ቁርኝት ጋር ያለው ልዩነት እያስደመመኝ ዓመት በዓል በመጣ ቁጥር ስለማስበው ነገር ማብሰልሰል ጀመርኩ - ስለ ዶሮ ወጥ።
Friday, September 2, 2011
የብክለት ወጥ
(ጌታቸው አሰፋ) አዲስ አበባ የመጀመሪያዋን መኪና ከዛሬ 104 ዓመት በፊት አስተናገደች - ታህሳስ 22 1889 ዓ.ም.። የታርጋ ቁጥሯ D3130 ነበር ተብሏል። አስር ሚልዮን ሕዝብ ያስተዳድሩ የነበሩት አጼ ምኒልክ ቴሌፎንን ወደ አገራችን ባስገቡ ከአራት ዓመት በኋላ ያስገቧት ነች። መጀመሪያ አለማማጃቸው፤ ከዛም እሳቸው፤ ከዛም ሾፌራቸው የነበረው ህንዳዊው ኤዳልጂ የነዷት መኪና ታወጣው የነበረ በካይ - ለምሳሌ ካርቦን-ዳይ-ኦክሳይድ - የአዲስ አበባን ንጹህ አየር በመቀላቀል አሃዱ ያለ አውቶሞቢላዊ በካይ ሆነ - የአገራችን የአካባቢ ብክለት ታሪክ ቅምሻ
Subscribe to:
Posts (Atom)