(ጌታቸው አሰፋ፤ የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ.ም.) ባለፈው እትም ስለ ሕንጻዎቻችን በጀመርነው ጽሑፍ ማጠቃለያ ላይ የሚገነባው እያንዳንዱ ሕንጻ በተቻለ መጠን ከሦስት የአካባቢ ክፍሎች አንጻር እንከን የለሽ ሆኖ መሠራት አለበት ብለን ነበር የፈጸምነው።
የመጀመሪያውና ዋነኛው ከምቹ ስፍራ ልኬት ጋር የሚገናኘው የሕንጻው የውስጠኛው አካባቢ ነው ብለን በውስጥ ምቾት ስር ስለሚካተቱት በቂ ብርሃን፤ ንጹህ አየር፤ ምቹ ሙቀት፤ሽታ አልባ፤ ድምጽና ኬሚካላዊ ልቀት የለሽ ስፍራ ስለ መፍጠር አንሰተን ነበር ያበቃነው። እስቲ ያዝ ካረግንበት እንልቀቀው።