(ጌታቸው አሰፋ፤ ግንቦት 11 ቀን 2004 ዓ.ም.) በአዲስ ጉዳይ መጽሔት በዚህ
የአረንጓዴ ጉዳይ አምድ የበኩር ጽሑፌን ከጻፈኩ እነሆ አንድ ዓመት ከሦስት ወር አለፈኝ። የጽሑፉ ማጠንጠኛ ዛሬም የተመለስኩበት
ርእስ የባዮዲዝል ነገር ሲሆን የተለያዩ ነጥቦች የተነሱበት ነበር። በአገራችን በቀጥታ ለሰው ምግብ ከማይውሉና ለባዮዲዝል ጥሬ እቃነት ይሆናሉ ከተባሉት ጥሬ እቃዎች መካከል
በዋናነት ጃትሮፋንና ጉሎን እንዲሁም በተወሰነ ደረጃ የፓልም ዘይት እንደሚገኙበት አይተን ነበር። በወቅቱ በነበረው መረጃ ወደ
ሰባ የሚጠጉ ባለሃብቶች ጃትሮፋን በማልማት ሥራ ላይ ለመሰማራት ፈቃድ ወስደዋል መባሉን፤ ከነዚሁ ወደ አሥራ አምስት የሚሆኑት ደግሞ ባለሀብቶች በደቡብ ኢትዮጵያ፤ በአማራ፤ በኦሮሚያ፤ በትግራይ፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በሶማሌ ክልሎች ውስጥ በመሥራት ላይ እንደሚገኙ እንደተነገረ
ወዘተ አንስተን ነበር።
Sunday, November 25, 2012
Tuesday, May 15, 2012
ኢል-ቆሻሻ
(ጌታቸው አሰፋ፤ ሚያዝያ 27 ቀን 2004 ዓ.ም.) የእጅ ስልክ፤ ቴሌቪዥን፤ የጠረጴዛ ኮምፒዩተር፤ የጭን ኮምፒዩተር፤ የስሌት ማሽን፤ አታሚ ማሽን ወዘተና ሌሎች በኤሌክትሮኒክ የሚሰሩ የቢሮና የቤት እቃዎች ሲያረጁ ወይም ከጥቅም ውጪ ሆነው ሲወገዱ ስለሚፈጥሩት ቆሻሻ ነው ዛሬ የምናነሳው። ኢል-ቆሻሻ እንበለው - የእንግሊዝኛውን በቀጥታ ወስደን ‘ኢቆሻሻ’ (ቆሻሻ ያልሆነ) ብለን ጥሩ ስም ከምንሰጠው።
የኤሌክትሮኒክ እቃዎች በዘመናችን በሰው ሕይወት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በእነሱ መጠቀም የጀመረ ሰው ከእነሱ ውጪ ሕይወት የሌለ እስኪመስለው ድረስ ጠባቃ ኑሮ እንደሚኖር ይታወቃል። አገራችን የእነዚህ ኤሌክትሮኒክ እቃዎች ለእያንዳንዱ ዜጋ ማዳረስ ቀርቶ በንጽጽር ከብዙ የአፍሪካ አገሮችም ባነሰ ደረጀ እንደሆነች ቢነገርም የኢል-ቆሻሻ መዘዝ ለማንሳት ግን ጊዜው አሁን ነው። Saturday, April 28, 2012
የት ፈጨሺው?
(ጌታቸው አሰፋ፤ ሚያዝያ 13 ቀን 2004 ዓ.ም.) በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በጾም ጊዜ የፍስክ ምግቦች ስም መጠራት የለበትም በሚል እሳቤ ላይ የተመሰረተ የልጆች (የወንድም የሴትም) ጨዋታ አለ። አንድ ልጅ ድንገት ተሳስቶ የፍስክ ምግብ ስም ከጠራ ሌሎች ልጆች ተሽቀዳድመው በቁንጥጫ ይይዙታል። ተቆንጣጩ ጾሙ ሲፈሰክ ለቆንጣጩ የሚሰጠውን የፍስክ ምግብ ጠርቶ ቃል ካልገባ አይለቀቅም። በዚህም ምክንያት ልጆቹ በጾም ወቅት ወሬ ሲያወሩ የፍስክ ነገር እንዳያነሱ መጠንቀቅ አለባቸው ማለት ነው። ይህን የፍስክም የጾምም ምግቦችን የሚያነሳው ጽሑፍ ለመጻፍ አስብ የነበረው ታላቁ የሁዳዴ ጾም ባለፈው ሳምንት ከመጠናቀቁ በፊት ነበር። ይሁንና የአንባቢያን ቁንጥጫ ፈርቼ ሳይሆን አዲስ ጉዳይ የቆየ ጉዳይን እየገፋብኝ ጾሙ ካለቀ በኋላ እነሆ ዛሬ ለመጻ(!)ፍ በቅቷል። እንቀጥል።
ኑ መረጃን እንሰብስብ፤ ተደራሽም እናድርገው
(ጌታቸው አሰፋ፤ መጋቢት 29 ቀን 2004 ዓ.ም.) ሰሞኑን በዝቋላ አቦ ገዳም ዙሪያ ያለውና አንድ ለአካባቢው የሆነው (ለአንድ ለእናቱ እንዲሉ) ግርማ ሞገሳሙ ደን በአሳዛኝ ሁኔታ ሲቃጠል ነበር (በጎግል ኧርዝ ካርታ ላይ ደኑን ፍንትው ብሎ ብታዩት አንድ ለአካባቢው የመሆኑ ነገር እጅግ ያሳሳችኋል)።ብዙ ሰው ከአዲስ አበባም ከደብረዘይትም እየተጠራራ ሄዶ ተጋግዞ አጠፋው - በእግዚአብሔር ቸርነት። ይሄ ነገር ከአሁን በፊት የተደጋገመ ክስተት በመሆኑ ለወደፊትም አንድ ነገር ካልተደረገ እንደገና ኧረ ከዛም በላይ ላለመከሰቱ ምንም ዋስትና የለም። እንደገና እንዳይከሰት ለማድረግ የተለያዩ ነገሮች መደረግ እንዳለባቸው በየቦታው ያለ ሰው ሲወያይ ነበር።
Monday, March 26, 2012
ማኅበራዊ አዛላቂነት
(ጌታቸው አሰፋ፤ መጋቢት 15 ቀን 2004 ዓ.ም.) አዛላቂነት ምጣኔ ሀብታዊ፤ አካባቢያዊና ማኅበራዊ አውታሮች አሉት። ማንኛውም ቴክኖሎጂ፤ ፕሮጄክት ፓሊሲ ወዘተ ከአዛላቂነት አንጻር ስንገመግመው ከእነዚህ ሦስት አውታሮች አኳያ በጎና ጎጂ ተፅዕኖውን ለይተን አስቀመጥን ማለት ነው። የማኅበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ መስክ በጣም ጠቃሚ ግን በጣም አስቸጋሪ መስክ ነው። የማንኛውም ልማት ጥቅም የሚለካው ተደምሮ ተቀንሶ ለሰው ከሚሰጠው
የአካባቢ ትምህርት ትላንትና ዛሬ
(ጌታቸው አሰፋ፤ መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ.ም.) ድሮ ድሮ በአጋጣሚ ካልሆነ በቀር ሆን ብሎ የአካባቢ ጉዳይን እንደ ትምህርት መስክ መርጦ መማር ብርቅ ነበር። እናም እኔ ወደ አካባቢ ጉዳይ መስክ የገባሁት የሆነ አጋጣሚ በፈጠረው አጋጣሚ የተነሳ ነበር። ከአስራ ሰባት ዓመታት በፊት እንዲህ ሆነ….
Wednesday, February 29, 2012
ከተማን እንደ ዘአካል
(ጌታቸው አሰፋ፤ የካቲት 17 ቀን 2004 ዓ.ም.) ዘአካል ማለት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የሚገለጽ ሰብሰብ ያለና የራሱ የሆነ አካል (የሚታይም የማይታይም) ያለው ህያው ማለት ነው - ኦርጋኒዝም የሚባለው ማለት ነው። ዘአካል ያድጋል፡ይራባል። ሲተነኮስ ግብረ መልስ የመስጠት ባህርይም አለው። ዘአካሎች ህያው ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያደርጋቸው ግብአት (ምግብና ኃይል0 ያስፈልጋቸዋል። እነዚህን ግብአቶች በአካባቢያቸው ከሚያገኝዋቸው ምንጮች ገቢ አድርገው ሲያበቁ በግንባንደት ሂደት (ሜታቦሊዝም) አካላቸውን እየገነኑ ወደ አካባቢያቸው ደግሞ ውጣት ይለቃሉ። ይህ ውጣት ጠጣር፡ፈሳሽ ወይም ጋዛማ ሊሆን ይችላል። ኃይልም ሊሆን ይችላል።
ማንኛውም ከተማም ህይወት
Subscribe to:
Posts (Atom)