(ጌታቸው አሰፋ፤ መጋቢት 15 ቀን 2004 ዓ.ም.) አዛላቂነት ምጣኔ ሀብታዊ፤ አካባቢያዊና ማኅበራዊ አውታሮች አሉት። ማንኛውም ቴክኖሎጂ፤ ፕሮጄክት ፓሊሲ ወዘተ ከአዛላቂነት አንጻር ስንገመግመው ከእነዚህ ሦስት አውታሮች አኳያ በጎና ጎጂ ተፅዕኖውን ለይተን አስቀመጥን ማለት ነው። የማኅበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ መስክ በጣም ጠቃሚ ግን በጣም አስቸጋሪ መስክ ነው። የማንኛውም ልማት ጥቅም የሚለካው ተደምሮ ተቀንሶ ለሰው ከሚሰጠው
Monday, March 26, 2012
የአካባቢ ትምህርት ትላንትና ዛሬ
(ጌታቸው አሰፋ፤ መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ.ም.) ድሮ ድሮ በአጋጣሚ ካልሆነ በቀር ሆን ብሎ የአካባቢ ጉዳይን እንደ ትምህርት መስክ መርጦ መማር ብርቅ ነበር። እናም እኔ ወደ አካባቢ ጉዳይ መስክ የገባሁት የሆነ አጋጣሚ በፈጠረው አጋጣሚ የተነሳ ነበር። ከአስራ ሰባት ዓመታት በፊት እንዲህ ሆነ….
Wednesday, February 29, 2012
ከተማን እንደ ዘአካል
(ጌታቸው አሰፋ፤ የካቲት 17 ቀን 2004 ዓ.ም.) ዘአካል ማለት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የሚገለጽ ሰብሰብ ያለና የራሱ የሆነ አካል (የሚታይም የማይታይም) ያለው ህያው ማለት ነው - ኦርጋኒዝም የሚባለው ማለት ነው። ዘአካል ያድጋል፡ይራባል። ሲተነኮስ ግብረ መልስ የመስጠት ባህርይም አለው። ዘአካሎች ህያው ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያደርጋቸው ግብአት (ምግብና ኃይል0 ያስፈልጋቸዋል። እነዚህን ግብአቶች በአካባቢያቸው ከሚያገኝዋቸው ምንጮች ገቢ አድርገው ሲያበቁ በግንባንደት ሂደት (ሜታቦሊዝም) አካላቸውን እየገነኑ ወደ አካባቢያቸው ደግሞ ውጣት ይለቃሉ። ይህ ውጣት ጠጣር፡ፈሳሽ ወይም ጋዛማ ሊሆን ይችላል። ኃይልም ሊሆን ይችላል።
ማንኛውም ከተማም ህይወት
Thursday, February 16, 2012
‘አረንጓዴ’ የሕንጻ ግንባታ
(ጌታቸው አሰፋ፤ የካቲት 3 ቀን 2004 ዓ.ም.) ባለፈው እትም ስለ ሕንጻዎቻችን በጀመርነው ጽሑፍ ማጠቃለያ ላይ የሚገነባው እያንዳንዱ ሕንጻ በተቻለ መጠን ከሦስት የአካባቢ ክፍሎች አንጻር እንከን የለሽ ሆኖ መሠራት አለበት ብለን ነበር የፈጸምነው።
የመጀመሪያውና ዋነኛው ከምቹ ስፍራ ልኬት ጋር የሚገናኘው የሕንጻው የውስጠኛው አካባቢ ነው ብለን በውስጥ ምቾት ስር ስለሚካተቱት በቂ ብርሃን፤ ንጹህ አየር፤ ምቹ ሙቀት፤ሽታ አልባ፤ ድምጽና ኬሚካላዊ ልቀት የለሽ ስፍራ ስለ መፍጠር አንሰተን ነበር ያበቃነው። እስቲ ያዝ ካረግንበት እንልቀቀው።
Friday, February 3, 2012
የሕንጻዎቻችን ጉዳይ
(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥር 19 ቀን 2004 ዓ.ም.) ሕንጻዎች ለሃምሳ ወይም ለስድሳ ዓመት ተብለው ይሰራሉ። ይሁን እንጂ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሕንጻዎች ከመቶ ዓመት በላይ ይቆያሉ። አንድ ትውልድ ማለት ሃያ አምስት ዓመት ማለት ስለሆነ አንድ ሕንጻ ቢያንስ ከተገነባበት ጊዜ ጀምሮ እድሜ ጠግቦ እስኪፈርስ ድረስ
ሰነድ ወደ መሬት ሲወርድ
(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥር 5 ቀን 2004 ዓ.ም.) የዛሬ ሁለት ሳምንት በወጣው ጽሑፌ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በደርባን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ይፋ ባደረገው በእንግሊዝኛ የቀረበው “የኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስልት” ሰነድ ላይ በመመሥረት የሰነዱን ይዘት በወፍ በረር ተመልክተን ነበር።
ለዛሬ በዚህ ሰነድና በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ውልጠት ዕቅድ ሰነድ ላይ ስለ ደን ጥበቃና ልማት የተባለውንና መሬት ላይ እየተደረገ ካለው ጋር እንመለከታለን።
‘የአይበገሬውና የአረንጓዴው ኢኮኖሚ’ ሰነድ
(ጌታቸው አሰፋ፤ ታኅሣሥ 21 ቀን 2004 ዓ.ም.)ቅድመ ነገር፡ እንኳን ለአዲስ ጉዳይ አምስተኛ ዓመት አደረሳችሁ። አዘጋጆችም እንኳን ደስ ያላችሁ። ወደ ዛሬው ጉዳይ ስንመለስ…
በኅዳሩ የደርባን ደቡብ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ወቅት ከተካሄዱት ነገሮች መካከል በኢትዮጵያ መንግሥት “ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ” በሚል ርእስ የተዘጋጀው ሰነድ ምረቃ ነው። በዛሬው እትም ስለ ሰነዱ ማንሳት
Subscribe to:
Posts (Atom)