(ጌታቸው አሰፋ)ድርቅ አጥቢያዊ መነሻና ምክንያት አለው። አሁን አሁን ደግሞ እንደ ሉላዊ አባባሽ ምክንያትና መነሻ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ(በካባቢ አየር ሙቀት መጨመር የሚገለጸው) ይጠቀሳል። ኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ መከሰት የጀመረው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ሰውኛ መንስኤው ይበልጥ እየተረጋገጠ ከመምጣቱ ቢያንስ መቶ ዓመታት በፊት ነው። በመፍትሔ ደረጃ አጥቢያዊ መነሻው ላይ ስናተኩር የሚጨበጥ ነገር ማድረግ እንችላለን። ሉላዊ መነሻችን እንደ አገር ብቻችንን በተናጠል ከኃሌ-ኵሉ ሆነን የምንፈታው አይደለምና። በዛ ላይ አጥቢያዊ ምንጩን ስናደርቅ ሉላዊ ድርሻችንን ተወጣን ማለት ስለሚሆን አሪፍ ነው።
ለእውቀት ያህል ግን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ በአንዳንድ ቦታዎች ድርቅን ሲያባብስ በሌሎች ቦታዎች ደግሞ የጎርፍ መጥለቅለቅን ያመጣል (ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ)።