(ጌታቸው አሰፋ፤ የካቲት 17 ቀን 2004 ዓ.ም.) ዘአካል ማለት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የሚገለጽ ሰብሰብ ያለና የራሱ የሆነ አካል (የሚታይም የማይታይም) ያለው ህያው ማለት ነው - ኦርጋኒዝም የሚባለው ማለት ነው። ዘአካል ያድጋል፡ይራባል። ሲተነኮስ ግብረ መልስ የመስጠት ባህርይም አለው። ዘአካሎች ህያው ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያደርጋቸው ግብአት (ምግብና ኃይል0 ያስፈልጋቸዋል። እነዚህን ግብአቶች በአካባቢያቸው ከሚያገኝዋቸው ምንጮች ገቢ አድርገው ሲያበቁ በግንባንደት ሂደት (ሜታቦሊዝም) አካላቸውን እየገነኑ ወደ አካባቢያቸው ደግሞ ውጣት ይለቃሉ። ይህ ውጣት ጠጣር፡ፈሳሽ ወይም ጋዛማ ሊሆን ይችላል። ኃይልም ሊሆን ይችላል።
ማንኛውም ከተማም ህይወት