(ጌታቸው አሰፋ) ታሪክ ሠሪም ባለ ታሪክም ነው ሰው - በሰፊው እንደሚታመንበት። እያንዳንዱ እሴት-አዘል ቁስም (ምርትና አገልግሎት) የራሱ የሆነ ታሪክ አለው - “ታሪከ ቁስ” ብንለውስ። አጭር ወይም ረጅም ሊሆን ይችላል። ጥሩም መጥፎም ሊሆን ይችላል።
የአንድ ምርት ወይም አገልግሎት ታሪክ ሲመረትና ጥቅም ላይ ሲውል የሚያልፍበትን ሂደት የሚያጠቃልል በጥንተ-ተፈጥሮ ምንጩ ጀምሮ በጥንተ-ተፈጥሮ ማረፊያው የሚያበቃ ሰንሰለታዊ ዑደትን የሚያጠቃልል ነው። ባለሁበት ዩኒቨርስቲ በዚህ ሰንሰለታዊ ዑደት ወቅት በአካባቢ አየር፤ ውኃና የብስ ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ የማስላትና የመገምገም ዘይቤ ነው “ወንበር ዘርግቼ” ጥናትና ምርምር የማደርገውና ትምህርትም የምሰጠው።