(ጌታቸው አሰፋ፤ ጥር 5 ቀን 2004 ዓ.ም.) የዛሬ ሁለት ሳምንት በወጣው ጽሑፌ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በደርባን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ይፋ ባደረገው በእንግሊዝኛ የቀረበው “የኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስልት” ሰነድ ላይ በመመሥረት የሰነዱን ይዘት በወፍ በረር ተመልክተን ነበር።
ለዛሬ በዚህ ሰነድና በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ውልጠት ዕቅድ ሰነድ ላይ ስለ ደን ጥበቃና ልማት የተባለውንና መሬት ላይ እየተደረገ ካለው ጋር እንመለከታለን።